የ2016 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የማስጀመሪያ መርሃግብር ተካሄደ

የካቲት 22/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኢንዱስትሪያሊዜሽን ለሃገር እድገት እና ህልውና ካለው ቁልፍ ሚና አንጻር የተቀረጸው “የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ በኢትዮጵያ የተሰሩ ምርቶችን ለአለም አቀፍ ተመልካቾች የማስተዋወቅ ትልቅ ሚና እንደነበረው የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል።

የገበያ ተደራሽነታቸውን የማስፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የመሳብ፣ አምራቾች እና የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በኢንዱስትሪው ውስጥ ባሉ ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብርን የማጠናከር የኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አላማ ይዞ የተነሣ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው አመት ያካሄድነው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የታለመለትን ዓላማ ያሳካ ነበር ያሉት ሚንስትሩ በየአመቱ ኤክስፖ መካሄዱ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች እንዳለው አስረድተዋል ።

የአትሌቲክስ ውድድር የሚካሄድበት፣ አምራቾች ምርቶቻቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ፣

አዳዲስ ምርቶችን እና ብራንዶችን የሚተዋወቅበት፣ ዘርፍ ለማሻሻል የሀገር ውስጥና የውጭ ባለድርሻ አካላት ውይይትና የልምድ ልውውጦች የሚያካሄዱበት ኤክስፖ መሆኑን ተናግረዋል ።

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post