በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 የሁለተኛ ቀን የፖናል ውይይት የተገኙ ግብዓቶች የአገር ውስጥ ምርትን በማጠናከር የምርት ጥራትን ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል

አዲስ አበባ 02/08/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የኢትዮጵያን ምርቶች በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ስትራቴጂዎችን በተመለከተ፣የሀገር ውስጥ ምርትን ከማስተዋወቅ፣ የምርት ጥራት ደረጃዎችን ከማሻሻል እና ጠንካራ የምርት ብራንዲንግ ጥረቶችን ከማዳበር ጋር የተያያዙ ቁልፍ የፖሊሲ መስኮች ተዳሰውበታል።

በኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የአገር ውስጥ ምርት በተለይም ተኪ ምርቶች ላይ በማተኮር የምርት ጥራት እና ምርትን ማስተዋቅና እና ብራንዲንግ ወሳኝ ጉዳዮችን የተመለከተው የኢትዮጵያ ታምርት 2016 ኤክስፖ ሁለተኛ ቀን የፖናል ውይይት ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ውይይቱን በመሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በፖናል ውይይቱ የተገኙ ግብዓቶች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን ተግዳሮቶች በመፍታት እና እድሎች በአግባቡ በመጠቀም በኢትዮጵያ የበለጸገ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን ለማጎልበት ተግባራዊ ግንዛቤዎችን ለመፍጠር የአገር ውስጥ ምርትን በማጠናከር የምርት ጥራትን ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እንዳለው መኮንን አዎያይነት ተወዳዳሪነት ለሀገር ዕድገት በምርት ጥራት ገቢ ምርትን መተካት በሚል ርዕሰ ጉዳይ የተከናወነው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 ሁለተኛ ቀን የፖናል ውይይት ላይ አቶ ገብረመስቀል ጫላ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ አቶ መላኩ አለበል የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ ዶ/ር ደረጀ እንግዳ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ የኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል እና ሕክምና አቅርቦት አምራቾች ማህበር ፕሬዝደንት ተወያዮች ነበሩ።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post