የ2016 ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የ2016 ኢትዮጵያ ታምርት ኤከስፖ የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ሚያዝያ 13/2016 እንደሚካሄድ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘላቂ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በ2014 በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ የተደረገው የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት ኢንዱስትሪውን ማሳደግና ተወዳዳሪ ማድረግ፣ ለአምራች ኢንዱትሪውን ምቹ የቢዝነስ ከባያዊ ሁኔታን መፍጠር እንዲሁም በሀገር ውስጥ ትላልቅ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመፍጠር መዋራዊ ሽግግሩ እውን እንዲሆን ታሳቢ ተደርጎ ንቅናቄው መጀመሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሚ/ዴታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገልጸዋል፡፡

የንቅናቄውን 3ኛ አመትን አስመልክቶ ከተዘጋጁ መርሃ ግብሮች መካከል የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ አንዱ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ታረቀኝ ዓላማውም አምራች ኢንዱስትሪዎች በስፖርቱ ዘርፍ መዋለ ንዋያቸውን አፍስሰው አስፈላጊውን ምርቶች በማምረት ድጋፍ እንዲያደጉ እና በሀገር ውስጥ አምራቾች የተመረቱ የስፖርት ዕቃዎችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም አስፈላጊውን የገበያ ትስስር ለመፍጠር ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑንም አክለዋል፡፡

የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫው መነሻና መዳረሻውን የሚያደርግ ሲሆን በሁለቱም ጾታዎች ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የ250,000.00 ፣የ150,000.00 ፣ የ100,000.00 የ50,000.00 እና የ25,000.00 የብር ሽልማቶች መዘጋጀታቸውን እንዲሁም በሁለቱም ጾታዎች በክለብ ደረጃ ተወዳድረው ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለሚወጡ ተወዳዳሪዎች የ100,000 ፣ የ75,000 እና የ50,000 የብር ሽልማት መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በእለቱም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተዋናዮች ፣አጋር ድርጅቶች ፣ከ 40 በላይ የአትሌቲክስ ክለቦችና መላው የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች በአጠቃላይ ከ10,000 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ላይ ሁሉም ማህበረሰብ ተሳትፎ በማድረግ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደረግ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post