የቱሪዝም ሚኒሰቴር አመራሮች እና ሠራተኞች የ“ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017”ን ጎበኙ
ሚያዚያ 28/2017 ዓ. ም (ኢሚ)የቱሪዝም ሚኒሰቴር አመራሮች እና ሠራተኞች ለ3ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን የ" ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017" ን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማእከል በመገኘት ጎብኝት አድርገዋል ።
በኤክሰፖ ጉብኝት ወቅት የማኑፋክቸሪንግ፣ የኢንዱስትሪ ውጤቶችና የማምረቻ ማሽኖች፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ፣ የእንጨት ውጤቶች እና በኢንዱሰትሪ የተቀነባበሩ የግብርና ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ 288 ያህል አቅራቢዎች ምርታቸውን በማቅረብ የተሳተፉ ሲሆን ኤክስፖ ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ነው ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት