የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ጉብኝት አካሄዱ
ሚያዝያ 28/2017 ዓ/ም
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አብዱረህማን አብደላ እንዲሁም መካከለኛ አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የተዘጋጀውን ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ጉብኝት አካሂደዋል፡፡
ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የሚቆየው ከሚያዝያ 25-29 /2017 ዓ/ም ነው፡፡