የገቢዎች ሚኒሰቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የ“ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017”ን ጎበኙ

የገቢዎች ሚኒሰቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የ“ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017”ን ጎበኙ

ሚያዚያ 28/2017 ዓ. ም ( የገቢዎች ሚኒስቴር )

በኢትዮጵ የሚገኙ በቁጥር ከ268 በላይ የሆኑ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የተሳተፉበት ኤክስፖ ከሚያዚያ 25-29/2017ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ለ3ኛ ጊዜ በተካሄደው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በሀገር ውስጥ አቅም የተመረቱ የኢንዱስትሪ ውጤቶችና የማምረቻ ማሽኖች፣ የጨርቃጨርቅና የቆዳ፣ የእንጨት ውጤቶች እና በኢንዱሰትሪ የተቀነባበሩ የግብርና ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

የኢትዮጵ ታምርት ኤክስፖ ዋና አላማ የአምራች ዘርፉን በማሳተዋወቅ፣ በሀገር ውስጥ ምርት ላይ መተማመንን በመጨመር የአምራች ዘርፉን ማበረታት እና የአምራች ዘርፉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚው የለውን አስተዋፅኦ ማሳደግ እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን በቀጣይም ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውጭ ምርት ጥገኝነት ማላቀቅ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Share this Post