የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017ን ጎበኙ።
ሚያዚያ 28/2017 ዓ/ም (ኢሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017ን ጎበኙ።
አቶ ማሙሻ ሀይሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሀላፊ ጉብኝቱ ለአመራሮች ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ምርት ከዓለም ሀገራት ጋር ተወዳዳሪ ለመሆን የሚደረገውን ጥረት በመረዳት በቁርጠኝነት ለስራ ለመነሳሳትና እንደ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያዮ ሀገር ውስጥ የተመረቱ የውሃ ፓምፖችንና ሌለሎች ማሽነሪዎችን ስራ ላይ ለማዋል የሚያስችል ግንዛቤ ስለሚፈጥር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
ለጎብኚዎቹ በሁሉም የኢንዱስትሪ ምርት ዙሪያ አምራቾችና የዘርፉ ባለሙያዎች ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት