በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የ2017 በጀት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ተመዝግቧል ፡፡

ጥር 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከተማ አስተዳደር ኢትዮጵያ ታምርት ስትሪንግ ኮሚቴ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ባለፋት 6 ወራት በጋራ ጥረት፣ በትብብርና ተቀናጅቶ በመስራት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበናል ሲሉ ገልፀዋል።

የውይይት መድረኩ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በመገምገም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተናበን እና ተቀናጀትን ለመስራት የጋራ መግባባት የምንይዝበት ነው ብለዋል ።

የኢትዮጵያ ታምርት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት አስተባባሪ አያና ዘውዴ (ዶ/ር) ገቢ ምርት በመተካት፣ የሃገር ውሰጥና የውጭ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በፋይናስ በአቅም ግንባታ ፣ በመሰረተ ልማትና በምርምር ስኬታማ ስራዎች በመስራቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል ።

በመጨረሻም በዕቅድ አፈፃፀሙ ወቅት የታዩ ጠንካራ ጎኖች፣ ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም የንቅናቄው የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት በማደረግና ለቀጣይ የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ የሚጠናቀቅ ይሆናል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post