የአምራች ኢንዱስትሪው 2017 በጀት ዓመት የዘርፉ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ 10.7% ማደጉ ተገለጸ።
ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ ታመነ የአምራች ኢንዱስትሪው 2017 በጀት ዓመት የዘርፉ የኢኮኖሚ ዕድገት ወደ 10.7% መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ አበባ በበጀት ዓመቱ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከሌሎች ዓመታት የተሻለ ስኬት ሊያስመዘግብ የቻለው መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
መንግስት አዲስ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ቀርጾ ወደ ትግበራ መገባቱና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።
የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስትራቴጅ ተቀርፆ በመስራቱ በበጀት ዓመቱ በክልል በሚገኙ ወረዳዎች 381 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተቋቁመዉ ዜጎች ተጨማሪ የስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ከኤክስፖርት አኳያ ሶስት መቶ አስራ ስምንት ሚሊየን ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት እንደ ተቻለና ከውጭ ይገቡ የነበሩ ምርቶችንም ሀገር ውስጥ በማምረትና በመተካት 4.5 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር የዉጪ ምንዛሬን ማዳን መቻሉን ገልፀዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት