በ2017 በጀት ዓመት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 318ሚሊዮን ዶላር በኤክስፖርት ገቢ ተገኝቷል(አቶ ዘሪሁን አበበ)

ሀምሌ 23/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጭ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አበበ በ2017 በጀት ዓመት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 318 ሚሊዮን ዶላር በኤክስፖርት ገቢ መገኘቱን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ለውይይት መነሻ የሚሆን የኤክስፖርት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ዘሪሁን አሁን ላይ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በየወሩ እስከ 28 ሚሊዮን ዶላር እንሚገኝና ከገበያ መዳረሻ አኳያም እስያ ከዩናይትድ ስቴትስና ከአፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ መያዟን ተናግረዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚው የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የኤክስፖርት አቅም ከፍ ለማድረግ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አንፃር የአቅም ግንባታ ስራዎችን መስራት፣ የግብዓት እጥረት ችግርን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መፍታት፣ ከጉምሩክ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን መቅረፍ፣ የድጋፍና ክትትል ስርዓትን ማጠናከር፣ የኤክስፖርት ማበረታቻ ስርዓትን መተግበርና ኤክስፖርትን የሚያጠናክሩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በገንዘብ መደገፍ በ2018 በጀት ዓመት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post