በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ከ4 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ግብይት የመፍጠር ስራ በተሳካ ሁኔታ ተፈጽሟል :: (አቶ መላኩ አለበል)
ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ማጠቃለያ መርሃ- ግብር የኤፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩንህ ፣ ከፍተኛ የመንስግት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሄደ።
የ2017 የኢትዮጵያ ታምርት ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በይፋ ከጀመረበት ከሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ፍፃሜው ባሉት 5 ቀናት ውስጥ የኤክስፖውን ዓላማ እና ግብ ያሳኩ ተግባራት መከናወናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የኢትዮጵያ የማምረት አቅም የታየበት እንደሆነ የገለፁት ሚኒስትሩ በኤክስፖው ከ120 ሺ በላይ ጎብኚዎች እንደተሳተፉና ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት የመፈፀም ዓላማውን ያሳካ እንደነበር ጠቁመዋል።
የኢንዱስትሪዎችን ማነቆ በጠንካራ ቅንጅት የመፍታት እና የፖሊሲ አማራጮችን የማየት ዓላማ ያለው የፓናል ውይይቶች አስተማሪ በሆነ መንገድ መከናወናቸውን አቶ መላኩ አክለዋል።
የምርት ልማት ውድድር እና solution talk, ኤክስፖውን በማድመቅና የኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ አዎንታዊ ሚናውን መጫወታቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ በተለይም እንደሀገር ያለንን የፈጠራ አቅማችንን አሳይቷል ሲሉ አክለዋል።
በተጨማሪም የማምረቻ መሳሪያዎችን በማምረት ወደ ገበያ የማስገባት ስራው የወደፊቱን የመልማት ተስፋችን፣ ከኋላ ተነስቶ ፈጥኖ የመድረስ የዲጂታል ዘመን ዕድል መጠቀማችን እና የባከነውን የማሸለብ ዘመን መሻገር መቻላችንን የሚያመላክት በፈጣን የዕድገት አዙሪት እየገባን መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እና ኤክስፖው በመጭው አመትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በተለይ ይህ የኢንዱስትሪያላይዜሽን ንቅናቄ የዝግጅት ምዕራፍን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቀ እና ወደ ተሟላ ትግበራ እየገባ በመሆኑ በመጪዎቹ አመታት የላቀ ውጤት ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ አቶ መላኩ ገልፀዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት