በ2017 በጀት ዓመት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ 672,190 ኪሎ ዋት ኃይል ማቅረብ ተችሏል (ወ/ሮ አበባ ታመነ)

ነሐሴ 16/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የስራ ስኬት ቁልፍ ሚና የሚጫወተው የኃይል አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ ለዘርፉ የአፈጻጸም ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኑነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሮ አበባ ታመነ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ መንግስት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው የኢከኖሚ ዘርፎች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ የገለፁት ስራ አስፈፃሚዋ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የተመዘገበውን የዘርፉን ስኬት በላቀ ሁኔታ ለማስቀጠል ፣ መዋቅራዊ በመሆነ አግባብ በቅንጅት የዘርፉን ችግሮች በጥናት በመለየት እና በመስክ የተደገፈ ምልከታ በማድረግ ዘላቂ መፍትሔ በማስቀመጥ በዘርፉ ቁልፍ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ ያለው ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ምክንያት ለአምራች ኢንዱስትሪው የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡

ወ/ሮ አበባ አክለውም አፈፃጸሙ ከባለፈው 2016 በጀት ዓመት ተመሳሳይ የዕቅድ አፈፃጸም ወቅት ጋር ሲነፃፀር 5.11 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ጠቁመው በ2018 በጀት ዓመት 675,500 ኪ/ዋት ኃይል ለማቅረብ በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚዋ አያይዘውም የዘርፉን የግብዓት አቅርቦት በማሻሻልና የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የማምረት አቅም አጠቃቀምን 70 በመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ተደራሽ በማድረግ ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ያላንን የተፈጥሮ እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ በመቀየር ፍትሃዊ የአኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስትራቴጅ ተቀርፆ በመስራቱ በበጀት ዓመቱ በክልል በሚገኙ ወረዳዎች 381 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተቋቁመዉ ለዜጎች ተጨማሪ የስራ ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post