በ2017 በጀት አመት ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የወጪ ምርት የተገኘው ገቢ የ8 በመቶ እድገት አሳይቷል::
ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ2017 በጀት አመት 11 ወራት 474.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ በአፈጻጸሙ 289.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም የዕቅዱ 61 በመቶ ማግኘት መቻሉን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘሪሁን አበበ ገልጸዋል፡፡
ይህ አፈጻጸም ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ከተገኘው አንጻር የ 22.2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወይም የ8 በመቶ ብልጫ እንዳለው መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸው በበጀት ዓመቱም መጨረሻ እስከ 315 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅና ይህም የ 25 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ወይም የ9 በመቶ እድገት ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡
ከአፈጻጸም አንጻር የምግብና መጠጥ ዘርፍ የተሸለ አፈጻጸም ያሳየና ከፍተኛ የኤክስፖርት አቅም እንዳለ ማየት ተችሏል ሲሉ አቶ ዘሪሁን አክለው ገልጸዋል፡፡
በቀጣይ ቀሪ ጊዜያትም በዘርፉ የታቀደውን ለማሳካት ትኩረት ተሰጥቶው እየተሰራ እንሚገኝም ስራ አስፈጻሚው አብራርተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት