የተኪ ምርት 2018ዓ.ም እቅድ እና የማምረት አቅም አጠቃቀም ስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

ሰኔ 3/2017ዓ.ም(ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት እንደገለፁት አንድ ዕቅድ አንድ አፈፃፀም በሚል መሪ ሃሳብ አየሰራን እንገኛለን ሰልጠናው የዚህ መሪ ሃሳብ አንድ አካል ነው ብለዋል።

በምርታማነት ፣ በማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ እና የ2018 ዓ.ም የተኪ ምርት ዕቅድ እና ስትራቴጂ ማስተግበሪያ ዙሪያ ግንዛቤ እና አቅም ለመፍጠር ለሁለት ቀን በሚቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ኢንዱስትሪዎች፣የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮ ባለሙያዎች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ናቸው ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post