የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረው የግምገማና የምክክር መድረክ ተካሄደ ።

ሰኔ 4/2017 ዓም(ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርት የ2018 ዓ.ም ዕቅድ ውይይቱን ያቀረቡት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኬሚካል ውጤቶች ዴስክ ኃላፊ አቶ መሃመድ ጦይብ እንደገለፁት ተኪ ምርት ዙሪያ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ውጤት እየታየበት ነው ብለዋል ።

በተኪ ምርቶች የ10 ዓመት ዕቅድ ነባራዊ ሁኔታውን ከ2013 አሰከ 2017 ዓ.ም በመዳሰስ የተኪ ምርት ዕቅድ መዘጋቱን ገልፀዋል ።

በተለይ በአምስት የአምራች አንዱስትሪው ንዑስ ዘርፎች 96 ተወዳዳሪ ተኪ ምርቶች ተለይተው በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፣ በኪሚካልና ኮንስትራክሽን ፣ ብረታብረት ብረት እና ቴክኖሎጂ ላይ በጥምረት የማሰተግበሪያ ዕቅድ ተዘጋጅቷል ያሉት አቶ መሐመድ በዘርፉ ከፖሊሲ እና ህግ ማሻሻያ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳይች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የሚፈታ ይሆናል ብለዋል ።

በማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የ10 ዓመት የልማት ዕቅድ አላማዎች በሃገር ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የዘርፉን ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የሚያስችል የተግባር አፈፃፀም በማዘጋጀት በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣የውጭ ምንዛሪ በማዳን፣ ከአካባቢ ልማት ጋር የተጣጣመ ኢንቨስትመንት በማስፋት፣ በሃገር ውስጥ ያለው ስትራቴጂያዊ አቅም በመጠቀም ተጨማሪ አሴት ያለውን የሃገር ውስጥ ምርት 60% በመቶ ለማድረስ አንሰራለን ብለዋል ።

በመጨረሻም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እድገታችን የኢትዮጵያን ማህበራዊ፣ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ በአስገዳጅነት የማስቀየር አቅሙን ታሳቢ በማድረግ እንደ ተግዳሮት የሚታዩትን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የየሴክተሮች ምርትና ምርታማነት ክፍተት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ክፍተቶች በመለየት ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በዕቅድ ውይይቱ ላይ የክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ቢሮዎች ፣ አምራቾች ፣ ተጠሪ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች ተሳትፈዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post