የ2018 በጀት ዋና ትኩረት ሁኔታ ቀያሪ ከሚባሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሞዴሎችን መፍጠር ነው። ( አቶ ዮናስ መኩሪያ )

ነሐሴ 15/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የግብአትና አቅርቦት ፣ የአቅም ግንባታና ምርምር ፣ የፋይናንስና ጉምሩክ ፣ የመሰረተ ልማት እና የኢንቨስትመንትና የግል ዘርፍ ጋር በተያያዘ ድጋፍ የሚያደርጉ 6 ክላስተሮች እንዳሉትና በዚህ አግባብ ስራዎች አየተሰሩ እንደሚገኝ የገለፁት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የአቅም ግንባታና ምርምር ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዮናስ መኩሪያ ባለው የአፈፃጻም ግምገማም በተለይም የንቅናቄው የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥሩ አፈፃጻም እንዳለው ባቀረቡት የ2018 በጀት አመት ዕቅድ የመነሻ ሁኔታ ገልፀዋል ።

ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ በ2018 የንቅናቄው ዋና የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ ከለያቸው ጉዳዮች መካካልም በአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል አማካኝነት ሁኔታ ቀያሪ ተብለው የተመረጡ 53 አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሚሰጣቸው መንግስታዊ ድጋፍ በተጫማሪም የውስጥ አቅማቸውን ለማሳደግ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ፣ የኢንዱስትሪዎቹን ነባራዊ ሁኔታ በማጥናት የሚስተዋሉ ክፍተቶችን የመድፈን እና መልካም ተሞክሮዎቻቸውን በማስፋት ሁኔታ ቀያሪ ተብለው ከተለዩት ውስጥ ሞዴል የሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መፍጠር ነው ሲሉ አቶ ዮናስ ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post