ለማህበረሰቡ ስለኢትዮጵያ ታምርት አክስፖ 2018 ዝርዝር መረጃ የሚስጥ ዌብሳይት ተዘጋጅቶ ተመረቀ

መጋቢት 2/2018 ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ከሚያዚያ 24 እስከ 28/2018 ዓ ም ለሚካሄደው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የለማ ዌብሳይት ለአምራቾች እና ለማህበረሰቡ ስለኢትዮጵያ ታምርት አክስፖ ዝርዝር የሚገልፅ እና አጠቃላይ መረጃ የሚስጥ ዌብሳይት ተዘጋጅቶ የተጠናቀቀ በመሆኑ ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልፀዋል ፡፡

ይህ ዌብሳይት በኤክስፖ ስለሚካሄዱ ሁነቶች (ኢቨንቶች) ሙሉ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም የኤክስፖ ቡዝ ምዝገባ ማካሄድ ፤ የኤቨንት የጊዜ ሰሌዳ ፤ የሴሚናር ምዝገባ ያካሂዳል፤ በተጨማሪም የጃክ ፖት ሎተሪ ያለው ሲሆን ሌላም ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል ፡፡

ኢትዮጵያ ታምርት ኢንዱስትሪ በሃገራችን እንዲስፋፋ እና እንዲያድግ ተወዳዳሪ እንዲሆን ምርትን በጥራት እና በብዛት ከማምረት አኳያ ትልቅ ለውጥ ያመጣ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

በዚህም ባለፉት ስምንት ወራቶች የኢንዱስትሪ ኤክስፖርት ከአርባ ፐርሰንት በላይ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን በተጨማሪም ከውጭ የምናስገባቸውን ምርቶች በሃገር ውስጥ በመተካት ለኢትዮጵያ ሁለተናዊ ለውጥ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 ዓ. ም 270 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን በኤክስፖው ዓለም አቀፍ ሴሚናሮች ፤ ፓናል ውይይት ፤ የገዢና ሻጭ ግንኙነት እና ከመንግስት አካላት ጋር ውይይት የሚካሄድበት የኢንዱስትሪ ሳምነት ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

ከኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በፊት ሚያዚያ 18/2018 የኢትጵያ ታምርት የ10 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የሚካሂድ ሲሆን በዚህም ከ17000 በላይ ሯጮች የሚሳተፋ ይሆናል።

Share this Post