የአፍሪካ የምግብ ስርዓት መድረክ 2024 (African Food System Forum 2024)
የአፍሪካ የምግብ ስርዓት መድረክ 2024 (African Food System Forum 2024) ላይ እየተሳተፉ ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ የመድረኩ ዋና አካል የሆነው ‘ዲል ሩም’ (Deal Room) ማስጀመሪያ ፓናል ላይ ንግግር አድርገዋል።
አቶ ሀሰን በንግግራቸው ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት የግሉ ዘርፍ ዋነኛው የልማት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት አጉልተዋል።
ከእነኝህም ማበረታቻዎች ውስጥ እንደ የግብር እፎይታ፣ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ መሆን እና የመሳሰሉ የፊስካል እና የጉምሩክ ጥቅማ ጥቅሞችን በዋናነት ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም መንግሥት ለንግድ ሥራ ማሻሻያ የሚያደርገውን ቁርጠኝነት በተለይም የመንግስት አገልግሎቶችን በዲጂታላይዜሽንና በማቀላጠፍ የኢንቨስትመንት ሁኔታን በእጅጉ አሻሽሏል ብለዋል። ለተቀናጁ አግሮ-ኢንዱስትሪያል ፓርኮች ደግሞ እንደ መንገድ፣ መብራት እና የውሃ ማጣሪያ ያሉ መሠረተ ልማቶችን አቅርቦት፣ እንዲሁም እንደ ኮንትራት እርሻ፣ ለወጣቶች እና ለሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ድጋፍን ጨምሮ ልዩ ድጋፍ እንደሚሰጥ አብራርተዋል።
በተጨማሪ ሚስንስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ ላይ በምግብ ማቀነባበር ዘርፍ ላይ መሰመራት ከሚፈልጉ አለም አቀፍ የግል ዘርፍ ባለሃብቶች ጋር የአንድ ለአንድ ስብሰባዎችን አድርገዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት