የአምራች ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት መጠን 3,165,220 ቶን ደርሷል
ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በ2017 በጀት ዓመት የአምራች ዘርፋን የተኪ ምርት መጠን 2,787,178 ቶን የምርት ለመተካት ታቅዶ 3,165,220 መተካት የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙንም ከ100% በላይ ማሳካት ተችሏል፡፡
አፈፃፀሙ በ2016 በጀት ዓመት ከተተካው 2,661,200 ቶን ጋር ሲነፃፀር 18.9% ጭማሪ አሳይቷል፡፡
የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች ፣ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ፣ የቆዳ አምራች ኢንዱስትሪዎች ፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርትን በማሳደግ የዕቅዳቸውን 100% ማሳካት የቻሉ ሲሆን በምግብና መጠጥ አምራች ኢንዱስትሪ ደግሞ የዕቅዱን 91.07% አስመዝግቧል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት