የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬ ውሎ የቀረቡለትን ሁለት አጀንዳዎች ማለትም በ4ኛ መደበኛ ስብሰባው የ3ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔንና መስከረም 28/2016 ዓ.ም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳሕለ ወርቅ ዘውዴ በሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ላይ ተገኝተው የበጀት ዓመቱን የመንግሥት የትኩረት እቅጣጫን አስመልክቶ ያቀረቡትን የድጋፍ ሞሽን መርምሮም በማጽደቅ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡

በዛሬው የምክር ቤት ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

Share this Post