በበጀት ዓመቱ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻን 44.84 በመቶ ማሳደግ ተችሏል፡፡

ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በ2017 በጀት ዓመት የአምራች ኢንዱስትሪን የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ 44.76 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ ማከናወን የተቻለው 44.84 በመቶ ሲሆን የዕቅዱን 100% በላይ በማሳካት አፈፃፀሙ ከአምናው በጀት ዓመት(2016) ከተመዘገበው 40.8 % ሲነፃፀር 9.9% በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በበጀት ዓመቱ የአምራች ኢንዱስትሪ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ ከማሳደግ አኳያ ዕቅዳቻውን ከ100% በላይ ማሳካት የቻሉት የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ፣ የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡

የጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ የቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች እንደቅደም ተከተላቸው የዕቅዳቸውን 97.4% ፣ 97.1% ፣ 98.9% ማሳካት ችለዋል፡፡

ለዕቅዱ መሳካት የሃገር ውስጥ ገበያ ድርሻን ለማሳደግ በመንግስት በኩል የሚፈፀሙ ግዥዎች በሃገር ውስጥ አምራቶች እንዲገዛ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ መደረጉ በምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡

አዲስ የወጣውን የመንግስት ግዥ አዋጅ ለማስፈፀም የተዘጋጀውን የማስፈፀሚያ መመሪያ መሠረት በማድረግ በተለይ የሀገር ውስጥ ግብዓትን በመጠቀም የተጨማሪ እሴታቸው የተሻለ እንዲሆን ለማድረግ የህግ ድጋፍ ስራዎች መከናወኑን የ2017 በጀት ዓመት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዕቅድ አፈፃፀም ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post