ከአምራች ኢንዱስትሪ ኤክስፖርት 450 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዷል።

ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2018 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪ ምርቶች ኤክስፖርት 450 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት በዕቅድ መያዙን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ ገልፀዋል፡።

ስራ አስፈፃሚው አክለውም ከእያንዳንዱ ንዑስ ዘርፍ አንፃርም በጨርቃጨርቅ 165,000,000፣ በምግብና መጠጥ 170,000,000፣ በቆዳ 50,000,000፣ በኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች 20,000,000 እንዲሁም በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ 45,000,000 ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት መታቀዱ አብራርተዋል።

በዘርፉ አዳዲስ ወደ ኤክስፖርት የሚገቡ ምርቶች በተመለከተ በጠቅላላው በበጀት ዓመቱ 15 አዳዲስ የኤክስፖርት ምርቶችን ለመላክ እና አዳዲስ የገበያ መዳረሻንን የማስፋት ስራ በዕቅድ መያዙን አቶ ጥላሁን ጠቁመዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post