ለአምራች ኢንዱስትሪው የቀረበው የሀይል አቅርቦት 50 በመቶ ከፍ ብሏል (ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (ኢሚ) መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማሻሻል በወሰደው እርምጃ የዘርፉ የግብዓት አቅርቦት እየተሻሻለ መምጣቱን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኃይል አቅርቦት ችግር 100% በሚባል ደረጃ መፈታት ተችሏል ብለዋል፡፡

ሀገራዊ የሀይል መሰረተ ልማት እድገቱ 47 በመቶ መሆኑን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ባሳለፍናቸው ስምንት ወራት የቀረበው የኃይል መጠን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃጸር 50 በመቶ ጭማሪ ጠቅሰዋል፡፡

ሀገራችን ብረት ስክራፕን አቅልጦ ለሚፈለገው ስራ በማዋል ረገድ 100 % በሚባል ደረጃ ላይ መድረሷንና የመስታወት የመቆራረጥና ቅርፃቅርፅ መስራት ተስፋ ቸጭ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረትና በተሰሩ ስራዎች የኢንዱስትሪ ዘርፉ የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ47 በመቶ ወደ 61 በመቶ መቻሉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካለን አቅም አንፃር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በያዝነው በጀት ዓመት ስምንት ወራት 55 አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ የገቡ ሲሆን 120 የሚደርሱ አምራቾች ወደ ዘርፉ ገብተው ስራ ለመጀመር ፈቃድ መውሰድ መቻላቸውንም ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post