የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀምን 56.04 ማድረስ ተችሏል(አቶ ጥላሁን አባይ)
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም የውይይት መድረክ ላይ የዘርፉን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ በኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ በተፈጠረ ቅንጅታዊ አሰራር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በተደረገ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም 56.04 በማድረስ የእቅዱን 93.4 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልፀዋል።
ስራ አስፈፃሚው አክለውም የማምረት አቅም አጠቃቀም ስኬቱ በ2015 በጀት ዓመት መጨረሻ ከተመዘገበው 55.79 የማምረት አቅም አጠቃቀም በያዝነው ግማሽ በጀት ዓመት የተመዘገበው 0.25 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ገልፀዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችንን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይከታተሉን
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት