የማምረት አቅም አጠቃቃም 70 በመቶ ለማድረስ በእቅድ ተይዟል ( (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ )

ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) በ2018 በጀት አመት በአምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ ከተያዙ እቅዶች መካከል የማምረት አቅም አጠቃቀምን 70 በመቶ ለማድረስ በእቅድ መያዙን የኢንዱስትሪ የእድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለጹ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2017 የዘርፉን አፈጻጸም ግምገማ እና በ2018 መነሻ እቅድ ላይ ለመወያየት ከተጠሪ ተቋማቱ እና ከክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ዘርፉ እስካሁን እያስመዘገበ ያለው አፈጻጸም ተስፋ የሚጣልበት ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ክልሎች ያቀረቡት አፈጻጸም አበረታች እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የእስካሁኑ አፈጻጸም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዘርፉን አቅም ይበልጥ ለማሳደግ ከፋይናነስ አቅርቦት አንጻር መሻሻሎች ቢኖሩም አሁንም ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ዘርፉ ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት ረገድ የ2017 አፈጻጸሙ የተሻለ እና ቀጣይነት ያለው መሻሻሎችን ያመጣ ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ሌላኛው ስኬት ከተመዘገባበቻው ስራዎች ውስጥ ተጠቃሽ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

የማምረት አቅም አጠቃቀምን ማሳደግ በዘርፉ እድገት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት አቶ ታረቀኝ ለአብነትም ኤክስፖርትን በማሳደግ፣ ለዜጎች የስራ እድልን በማመቻቸት እና ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርትች ለመተካት ከሚደረገው ጥረት አንጻር የታለመውን በማሳካት ረገድ እስተዋጽዎ የጎላ በመሆኑ የማረት አቅም አጠቃቀም ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post