ከህዳሴው ግድብ ሁለት ተርባይኖች 750 ሜጋ ዋት በማመንጨት ህረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 13ኛ ዓመት "በህብረት ችለናል" በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል ።

ግድቡ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝና ግንባታው አሁን ላይ 95 ነጥብ 8 በመቶ ላይ መድረሱንና በተከታታይ የውሃ ሙሌቱን በማከናወን በአሁኑ ወቅት ከ 42 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ መያዙን የመረጃ ምንጮች ያመላክታሉ፡፡

ለውጡን ተከትሎ በተሰጠ አመራር ከህዳሴው ግድብ ሁለት ተርባይኖች 750 ሜጋ ዋት በማመንጨት ህዝቡን የጥረቱ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

የግድቡ መጠናቀቅም የአምራች ኢንዱትሪውን የኃይል አቅርቦት ተግዳሮቶች በመቅረፍ ምርትና ምርታማነትን እና የውጪ ምንዛሬ ገቢ መጠንን በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

በአስካሁኑ የግድቡ ግንባታ ሂደትም ክህብረተሰቡ ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ከህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ የሚያመላክታል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post