በበጀት ዓመቱ 8.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል (አቶ መላኩ አለበል)
ሀምሌ16/2017 ዓ.ም(ኢ.ሚ) የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም ሀገራዊ የልማት ዕቅድን፣ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና የ2018 የአምራች ኢንዱስሪ ዘርፉ መነሻ ዕቅድ ዙሪያ ከአጠቃላይ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት እንደ ሀገር ሁሉን አቀፍና በተቀናጀ አግባብ በተሰራው ውጤታማ ሀገራዊ ስራ 8.1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ እንደ ተገኘ በመጥቀስ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ 318,279,100 የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ገልፀዋል ፡፡
አቶ መላኩ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ በመተግበሩና የአምራች ኢንዱስትሪ ብሔራዊ ካውንስሉ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት በዘርፉ ውስጥ ያሉትን ማነቆዎች መለየትና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የመፍትሄ እርምጃ መውሰድ ዘርፉ የተሻለ ሀገራዊ ዕድገት ማስመዝገብ እንዲችል ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት