የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተጠሪ ተቋማትና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎች የ9 ወራት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጀመረ
ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በካይዘን የልህቀት ማዕከል በመካሄድ ላይ ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ቀመድረኩ እንደገለፁት ባለፉት 9 ወራት በአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ በአዳዲስ ኢንቨስትመንት ማስፋት፣ በኢንዱስትሪ ሽግግርና ጥናትና ምርምር ስራዎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዎል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉ ሞተር በማድረግ ዘርፉን ለማነቃቃት በታቀደው መሠረት የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ ነበሩ ያሉት ሚኒስትሩ በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪ ዋነኛው ሀገራዊ የርብርብ ማዕከል እንዲሆን አስችሏል ሲሉ ገልፀዎል።