"በበጀት አመቱ 9 ወራት ከ10.8 ሚልየን ቶን በላይ ግብዓት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ቀርቧል።

ግንቦት 06/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር ባለፉት 9 ወራት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ከ10.8 ሚልየን ቶን በላይ ግብዓትን ማቅረቡን የተቋሙ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን አባይ አስታወቁ።

የሚኒስቴሩን የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ጥላሁን በተጨማሪም በ9 ወራት ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት በተሠራው ስራ 1.96 ቢልየን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት መተካት መቻሉን ገልፀዋል።

ስራ አስፈፃሚው በዚሁ ሪፖርታቸው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ለስራ ማስኬጃና ለማሽነሪ ሊዝ አገልግሎት የዋለ 44.22 ቢልየን ብር ብድር መቅረቡን አስታውቀዋል። ከዚህ ውስጥም 4.9 ቢልየን ብሩ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የቀረበ ነው ብለዋል።

አቶ ጥላሁን አያይዘውም የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም ከማሻሻል አንፃር በተከናወነ ሠፊ እንቅስቃሴ ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ማምረት አቅማችን 56.04 መድረሱን ገልፀው በዘርፍ ደረጃ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም 64.8 በመቶ ማድረስ ሲቻል የቆዳ 58.9፣ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ 40.1፣ የምግብና መጠጥ 62፣ እንዲሁም የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓት አምራቾች ደግሞ 54.3 በመቶ መድረሱን አብራርተዋል።

Share this Post