የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ሀሰን ሙሀመድ በአቶ ጆናታን ሰይድ የተመራው አሊያንስ ፎር ኤ ግሪን ሪቮሊዩሽን ኢን አፍሪካ (AGRA) ከፍተኛ ልዑካን ቡድንን ተቀብሎ ተወያይቷል።

የግብርና እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎችን ከኢትዮጵያ የልማት ግቦች ጋር በማያያዝ ማጠናከር ላይ ያተኮረ ዉይይት አድርገዎል። አርሶ አደሮችንና ኢንዱስትሪዎችን ማስተሳሰር፣ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ እና የአቅም ግንባታ ውጥኖችን ማሳደግን ጨምሮ የትብብር እድሎች ላይ ተወያይተዋል።

AGRA የኢንዱስትሪው ሪ ዘርፉን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው የገለፀ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች የተወሰኑ የድጋፍ መስኮችን በመለየት ተቀራርበው ለመስራት ቁርጠኞች መሆናቸውን ገልጸዉ በኢትዮጵያ ዘላቂ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልማት ተስፋ ሰጪ አጋርነት መጀመሩን እንደሚያሳይም ተናግረዎል።

ይከታተሉን

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post