የጃፓን ዓለም አቀፍ ካይዘን ማህበር(JICA)ና የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ(AUDA-NEPAD ለአፍሪካ ኢንዱስትሪዎች ልማት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በተመለከት የውይይት መድረክ ተካሄደ
የካቲት 8/2016 ዓ.ም (ኢሚ) አዲስ አበባ ከካይዘን ለህቀት ማዕከል የጃፓን ዓለም አቀፍ ካይዘን ማህበር(JIKA) የካይዘንን ፅንሰ ሀሳብ በአፍሪካ አህጉር ለማስረፅና ለመተግበር የተጓዘባቸውን የትግበራ ሂደቶችና ያመጣቸውን ውጤቶች የሚመለከት በርካታ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ጃይካ ለአፍሪካ ኢንዱስትሪዎችና ልማት ላበረከታቸው አስተዋፅኦዎች ዕውቅና መስጠት ዓላማው ያደረገ የውይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ በአፍሪካ አህጉር የካይዘንን ፅንሰ ሃሳብን በማስረፅና ትግበራውን በማላመድ በኩል የነበሩ ተግዳሮቶችና ፍልስፍናው ለኢንዱስትሪዎች ዕድገት ያመጣው ፋይዳ የተብራራ ሲሆን ጃይካ ኢትዮጵያ ውስጥ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የካይዘን ንቅናቄ በተሻለ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ የጃፓን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉካዛዋ ዮይቺን ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጄንሲና የጃፓን ዓለማቀፍ ካይዘን ማህበር እንግዶች ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
ይከታተሉን
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት