በኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ የተመራ ሰባተኛው የቆዳ ተነሳሽነት ለዘላቂ የሰው ሀይል ልማት/leather industry for sustainable employment Cerastion / ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይቱ በቆዳው ዘርፍ ያሉ ዋናዋና ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በተለይም ጥሬ ቆዳ ጥራትና አሰባሰብ፣የቆዳ ኢንዱሰትሪዎች የማምረት እቅም ፣አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት እና የገበያ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንዲሁም በመንግስት ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ የሚገኘው የሞጆ ሌዘር ሲቲ ፕሮጀክት አፈጻጸም በውይይቱ ተነስቷል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤት አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በሞጆ ከተማ የተሟላ የሳተላይት ላብራቶሪ መሰራቱን ጠቁመዉ መጋቢት ወር ላይ ስለሚመረቅ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል፡፡
ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የሞጆ ሌዘር ሲት ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ አሁን ያለውን የቆዳ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እና ምቹ ለማድረግ ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ፕሮጀክቱ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ በስራ ላይ ያለው የፕሮጀክቱ ኮሚቴ የአዋጭነት ጥናቱ በፍጥነት እንዲጠናቅ መመሪያ ሰተዋል፡፡
በውይይቱ የሞጆ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ፣ከግብና ሚኒስቴር፣ከገንዘብ ሚኒስቴር ከአውሮፓ ህብረት እና ሌሎችም አካላት ተሳትፈውበታል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት