7ኛው የአግሮ ፉድ ሾው ፎረም ተካሄደ

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) 7ኛው የአግሮ ፉድ እና ፕላስቲክ፣ህትመት፣ፓኬጅ የምግብና ቡና ሾው ተካሄ።

ፎረምን በንግግር የከፈቱት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ ፎረሙ የማሽነሪ፣ የቁሳቁስ እና የማሸጊያ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ በኢትዮጵያ እየታየ ላለው ለውጥ፣ ግብርናና ኢንዱስትሪ የሚቆራኙበት፣ ኢንዱስትሪው ሁሉን አቀፍ የሀገራችን የዘላቂ ልማት ሞተር መሆኑን የሚያሳይ ነዉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው ባሉ ፓርኮች ትስስር፣ እየቀረፀች ባለው ተስማሚ ፖሊሲዎች እና ንቁ የሀገር ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ተሳትፍ እያደገች የአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መገኛ በመሆኗ ኩራት ይሰማናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዘርፉን ችግሮች በመፍታት የአምራች ኢንዱስትሪው ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክተውን ድርሻ ከፍ ለማድረግ የምግብ እና መጠጥ ማቀነባበሪያ ሴክተሩ በአፍሪካ ውስጥ በፍጥነት እያደገ የመጣውን ፍላጎት ለማሟላት የአገር ውስጥ ምርትን ለማጠናከር፣ ምርታማነትን ለማጎልበት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት እና እሴትን የተጨመረባቸውን ምርቶች ወደ ውጭ ዓለማቀፋዊ ተወዳዳሪነታችንንና ተፈላጊነታችንን ከፍ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገራችን የብልፅግና ራዕይ ስኬት እውን ማድረጊያ መንገድ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታው እንደ መንግስት መሠረተ ልማትን ማጠናከር፣ የንግድ ሥራን ቀልጣፋናምቹ አድርጎ ማሻሻል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በምግብ ማምረቻ፣ በማሸግ እና በሎጂስቲክስ ስራዎች ላይ እሴት መጨመርን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሁነቱ የእርስበርስ ግንኙነት ለመገንባት፣ እውቀትን ለመለዋወጥ፣ በኢኮኖሚ የመለወጥ የጋራ ግቦቻችን ላይ ለመድረስ፣ ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪ እድገት ለማሳካት እና ክልላዊ ውህደት አጠናክሮ ለማስቀጠል አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስፈነጥር እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

በሁነቱ ላይ ከ15 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ኤግዚቢተሮች እና ልዑካን ተሳትፈዎል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post