የግሪን ኮል ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋልና በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈረመ፡፡

መጋቢት 23/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዲስትሪ ሚኒስቴር ከግሪን ኮል ኢትዮጵያ እና ከዳንጎቴ ጋር የግሪን ኮል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ለማዋልና በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በማስተባበርና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንዲሰጥ የግሪን ኮል ኢትዮጵያ የግሪን ኮል ቴክኖሎጂ ኢንዲያመርት እንዲሁም ዳንጎቴ ምርቱን እንዲጠቀም የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዋናነት ስምምነቱ ትኩረት የሚያደርገው አማራጭ የኃይል አቅርቦትን በማስፋት ፣ የስራ ዕድል በመፍጠር ፣ ወራሪ አረሙን በማስወገድ ለአማራጭ የኃይል ምጭነት በመጠቀም ለአካባቢዊ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማመቻቸት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅኖን በመቀነስ ለአምራች ኢንዱስትሪ አማራጭ ኃይል ለማቅረብ በጋራ ለመስራት መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

Share this Post