አቶ ሀሰን መሐመድ በኢትዮጵያ የማሌዥያ ኤምባሲ ልዑክ ጋር ተወያዩ፡
መስከረም 18/2018 ዓ.ም (ኢሚ) በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሐመድ በኢትዮጵያ የማሌዥያ ቋሚ ጉዳይ አስፈጻሚ (chargé d'affaires) ሞህድ አፋንዲ አቡበክር የተመራ ልዑክቡድንን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡
በማሌዢያ መንግስት እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመከባበር ላይ የተመሰረተ አጋርነትን ያረጋገጠ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ብቻ ሳይሆን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ልማት ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነት መኖሩን ጠቁመል፡፡
የማሌዢያ በኢንዱስትሪ ለውጥ፣ ኤክስፖርት ማስተዋወቅ እና በአለም አቀፍ ንግድ ተወዳዳሪነት ያስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም ዙሪያ በሰፊው የሚታወቅ ነው ያሉት አቶ ሀሰን መሐመድ በቅርቡ የማሌዢያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ መከፈቱም ኢትዮጵያ በፈጣን ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ ጎዳና ላይ ያለች ሀገር እንደመሆኗ ኢትዮጵያ ከማሌዢያ ልምድ ለመቅሰም ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጠር ጠቁመዋል፡፡
በኢትዮጵያ ስላለው የንግድና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ እና በሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርም ትኩረት ስለተሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ለልዑክ ቡድኑ ገለፃ ተደርጓል፡
በኢትዮጵያ የማሌዥያ ቋሚ ጉዳይ አስፈጻሚ (chargé d'affaires) ሞህድ አፋንዲ አቡበክር በበኩላቸው ማሌዥያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡