የጠላቶቻችንን አጀንዳ ተቀብለው መለያየትን ከሚሰብኩ ክፉዎች ተጠብቀን መለያችን የሆነውን አንድነታችን እናፅና (አቶ መላኩ አለበል)

መጋቢት 6/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በተገኙበት የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ፣ የአምራች ኢንተርፕራይዝ ልማትና የአምራች ኢንዱስትሪ አመራሮችና፣ስራተኞች እና የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖች ጋር የኢፋጣር መርሃ - ግብር አካሂዷል ።

በመረሃ ግብሩ ላይ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገነት በሚከፈትበት ሲኦል በሚዘጋበት በዚህ የተቀደሰ ወር ይህን የኢፍጣር መረሃ ግብር ከእናንተ ጋር በማክበሬ ትልቅ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።

የኢፋጣር መረሃ -ግብር ያዘጋጀነው ከእስልምና እምነት ወድሞቻችን ጋር ያለንን ፍቅር፣ አብሮነት እዲሁም መተሳሰብ ለመግለፅ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህ ዓይነቱ መርሐ-ግብር የሰራተኞችን እና የኃላፊዎችን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከር የሥራ አካባቢን ምቹ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ከመሆኑም በላይ ልምዶችን ለመለዋወጥ እድል ይፈጥራል ብለዋል ።

የጠላቶቻችንን አጀንዳ ተቀብለው መለያየትን ከሚሰብኩ ክፉዎች ተጠብቀን መለያችን የሆነውን አንድነታችን እናፅና ያሉት አቶ መላኩ ፍቅርና አንድነትን የሚያጠናክሩ የአብሮነት ባህላችንን የሚያጎለብቱ ተግባራት የእለት ከእለት ስራዎቻችን መሆን አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል ።

ኢትዮጵያ ታምርት ብለን የጀመርነው ንቅናቄ ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስራን ባህል አድርጎ በየተሰማራበት በታማኝነት እና በሃገር ፍቅር ስሜት መስራት አለበትም ሲሉ ገልፀዋል።

በኢፋጣር መርሃ - ግብሩ ላይ የተሳተፉ የስልምና እምነት ተከታዮች በበኩላቸው ተቋሙ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣቱ እንዲሁም ክርስቲያን የተቋሙ ባልደረቦች ላሳዩት አብሮነትና ፍቅር አመስግነዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post