የኢትዮጵያ ታምርት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እድገት መሰረት እየጣለ ነው( ወ/ሮ አበባ ታመነ)

መጋቢት 04/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉን ማነቆዎች በተባበረ ክንድ በመፍታት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ቀዳሚ የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ ዓለማ በመሰነቅ የተጀመረ መሆኑን የጠቆሙት የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ ታመነ ንቅናቄው በ2014 ዓ.ም በክቡር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ከተጀመረ ጀምሮ ዘርፉ በሀገር ደረጃ ቅድሚያ ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ እንዲሆን ማስቻሉን ጠቁመዋል ።

የመንግስት ተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራር በማሻሻል፣ የዘርፉን ችግሮች በየደረጃ እየለየ በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚፈታ የክላስተር አደረጃጀትና የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎችን ከብሔራዊ የኢኮኖሚ አበርክቷቸው አንፃር እየለየ በስራ ሂደት የሚገጥሟቸው ችግሮች በሚመለከተው ተቋም በአፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኝ የሚያደርግ ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ተቋቁሞ እየሰራ ስለመሆኑም ገልፀዋል ።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ራዕይ ለማሳካት በሚደረገው ጥረት አምራቾችን ለማስተዋወቅ ፣የእርስበርስ ትስስር ለመፍጠር፣ የገበያ ትስስር፣ የእውቀት ሽግግር መፍጠር የሚያስችል ዓመታዊ ኤክስፖ የሚያካሂድ መሆኑን ጠቁመዋል ።

ሀገራዊ ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪው በመንግስት የቅድሚ ትኩረት እንዲያገኝ በማስቻልና አምራቾችን በማስተዋወቅ የአምራቾችን ችግሮች በተቀናጀና በተናበበ መንገድ በመፍታት ዘርፉ የተጣለበትን ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲያሳካ ለማስቻል በሚደረገው ጥረት ፍሬ እንዲያፈራ መሠረት እየጣለ ነው ብለዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post