የአምራች ኢንዱስትሪዎችንየኃይል አቅርቦት ችግር መቶ በመቶ ሊባል በሚችል ደረጃ መፍታት ተችሏል ( ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ)
መጋቢት 11/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ዘርፉ የኢኮኖሚ ድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
በተያዘው የ2017 በጀት አመት በዘርፉ በተግዳሮትነት የተቀመጡትን የውጪ ምንዛሬ ፣ የግብአት እና የኃይል አቅርቦት ጥያቄዎች መሻሻል ማሳየቱንም ጠቁመዋል።
የኃይል አቅርቦትን በተመለከትም በተያዘው በጀት አመት በፋብሪካዎች የሚስተዋል ችግሮችን መቶ በመቶ ሊባል በሚችል ደረጃ መፍታት መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።
በተያዘው የ2017 በጀት አመት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 50 በመቶ ተጨማሪ መቅረቡንና አቅርቦቱ ማደጉን የጠቆሙት ሚኒስትሩ በቀጣይም በየአመቱ በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ ተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት