ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ‼️

"በግብርና ምርት የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ደርሷል፣

በስንዴ ልማትም በመኸር 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር፤

በበጋ መስኖ ልማት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ተሸፍኗል፣

በዚህም ከ300 ሚሊየን ኩንታል ያላነሰ ምርት ይስበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፣

በቡና እና ሻይ ምርትም የተሻለ ስኬት ተመዝግቧል፣

ባለፉት ስምት ወራት ብቻ ከቡና ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሰብሰሃራ እድገት 4 ነጥብ 2 ይሆናል ብለው ገምተው ነበር።

ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 4 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ችላለች፣

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ታይተው የማይታወቁ ውጤቶች ተመዝግበዋል

የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሰብል ሽፋን ከ17 ነጥብ 5 ሚሊዮን ወደ 20 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ማደግ ተችሏል፣

ዛሬ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ስንዴ አምራች ሀገር ነች

በስንዴ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ዘርፎች የመጣው እምርታ ይበል ይቀጥል የሚያስብል ነው

ለምሳሌ ቡና በለውጡ ማግስት 700 ሚሊዮን ገደማ በዓመት ኤክስፖርት እናደርግ ነበር፣

በቡና ኤክስፖርት ባለፉት ስምንት ወራት ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በታሪክ አይታው የማተውቀው ውጤቶች አስመዝግባለች

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post