ኢንዱስትሪ ለአንድ ሃገር የእድገት ኃይል ነው (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)
መጋቢት12/7/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የዘረፍን እንቅስቃሴ ለህብረተሰቡ ተደራሽ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
በሃገራችን ጠንካራ አምራች ኢንዱስትሪ ዎችን ለማሳደግ ዕውን ሆኖ አበረታች ለውጥ እያስመዘገበ ያለውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ዓላማ ለማሳካት የተቀየሱ እስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች መሰረት በማድረግ ዘላቂና ውጤታማ የኮምንኬሽን ስራ ማከናወን እንዲቻል የአምራች ኢንዱስትሪ የሚዲያ ፎረም በመመስረት በቅርበትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ።
ሚኒስቴር ዴኤታው አክለውም በየዘርፉ የሚወጡ ፖሊሲ ፣ የማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎች፣ ህጎችና መመሪያዎች የታለመላቸውን ራዕይ በማሳካት ለሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ፣ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዕድገት አውንታዊ ሚና እንዲኖራቸው ለማስቻል ሚዲያ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል ።
ተኪ ምርቶች ላይ ውጤታማ ለመሆን አገር በቀል ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥን በመስራት የውጭ ምንዛሪ ከማዳን በላይ የሃገርን ሉዋላዊነት ከማሰከበር አንፃር ፋይዳው የጎላ ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ህብረተሰቡ በሀገሩ ምርት በኩራት እንዲጠቀም ለማስቻል ሚዲያው የግንዛቤ ማስጨበጡን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል ።
በመጨረሻም ሚኒስትር ዴኤታው የሚዲያ ፎረም ምስረታው ዋና ዓላማ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ዕድገት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የላቀ የአግልግሎትና ድጋፍ መስጠት የሚችል ውጤታማ የአስራር ስርአት በመዘርጋት የሰው ሃብትና የቴክኖሎጂ አቅሙ የላቀ ደረጃ ላይ የደረሰና የሀገራችን ተቀዳሚ የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነ የአምራች ኢንዲስትሪ በመፍጠር በራሱ ምርት በመኩራት የሚጠቀም ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚዲያ አጋርነትን ማረጋገጥ ነው ብለዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት