የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የአምራች ኢዱስትሪው ሚና ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፓናል ውይይት ተካሄደ ፡፡

መጋቢት 24/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችጋር ለኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ስኬት የአምራች ኢዱስትሪው ሚና ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ የፓናል ውይይት አካሄደ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄን የጀመረውና የንቅናቄው አካል የሆነው ዓመታዊ ኤክስፖ የሚከናወነው ለዘላቂ ልማት እና ተወዳዳሪነት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሀገራዊ ስርዓት በመዘርጋት አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለሃገር በቀሉ ኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬት እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማስቻል መሆኑን በኢትዮጵያ ታምርት የአቅም ግንባታ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዮናስ መኩሪያ ገልፀዋል፡፡

የንቅናቄው ምሶሶዎች የሃገር በቀል ምርቶች እና አምራቾችን ማጠናከር ፣ የኢንዱስትሪያል ማህበረሰብ ግንባታን ማሳደግ ፣ መሪ ኢንዱስትሪዎችን መፍጠር ፣ ምቹ የቢዝነስ ከባቢ መፍጠር እና የጥናት እና ምርምር ችግር ፈቺነትን ማሳደግ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ዮናስ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የዘርፉን ዕድገት ለማሳካት በባለቤትነት እና በተቀናጀ አግባብ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለመ የ10 ዓመት ንቅናቄ ነው መሆኑን ገልፀው ኤክስፖው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማነቃቃት እና ለመደገፍ ያለመ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል ነውም ብለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ሚያዚያ 19 የሚካሄድ ሲሆን አስራ ሶስት ሺህ ሰዎች በሩጫ እደሚሳተፉ ይጠበቃል ፡፡

በሌላ በኩል ከሚያዚያ 25 አሰከ 29/2017 ዓ.ም በአዲስ አለም ዓቀፍ ኮንቬንሸን ማዕከል በሚካሄድው ኤክስፖ 2017 ከ220 በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉና ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች በላይ ኤክስፖውን ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ በምክክር መድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post