የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የአምራች ኢንዱስትሪዎችን እየጓበኙ ነው
መጋቢት 26/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን የሀገራችን ተቀዳሚ የኢኮኖሚ ምንጭ በማድረግ የማይናጋ መሰረት ያለው ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን አውን ለማድረግ የዘርፉን ችግሮች በተቀናጀ መልኩ ለመፍታት እየተሰራ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄን በማስጀመር ባሳለፍናቸው ሶስት ዓመታት ንቅናቄው በፈጠረው ቅንጅታዊ አሰራርና ዘርፉ በሁሉም የመንግስት መዋቅሮች ትኩረት እንዲሰጠው በማድረጉ ተስፋ ሰጭ ስኬቶች እየተመዘገበ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመጡ ለውጦችንና የዘርፋን የስራ እንቅስቃሴ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እየጎበኙ ነው።
ዘደይ አግሮ ኢንዱስትሪ የማር ማራት እና ቢኤም ኤፍ ባህላዊ እና ዘመናዊ አልባሳት ማምረቻ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን በቀጣይም ሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎችን ይጎበኛሉ ።