የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ታምርት ክላስተሮች ጋር እየተወያየ ነው።
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ታምርት ክላስተሮች ጋር የ2017 በጀት ዓመት የ8 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ውይይት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤታማ ለማድረግ የነበሩ ችግሮችን በመለየት የቅንጅት አሰራርን ለማሳደግ፣ የስራ ዕድል ለመፍጠር እና ለቀጣይ ዓመት ዕቅድ መሳካት የሚያስችሉ ውይይቶች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት