የተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ለዘርፉ መነቃቃት እየፈጠረ ነው ።

ሚያዚያ 18/2016ዓ.ም(ኢ.ሚ)በተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች የማዕድንና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች እና አባላት ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የተሻሻለው የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በዘርፉ ላሉ ባለሃብቶች መነቃቃት መፍጠር መጀመሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ።

የ10 ዓመቱ የኢንዱስትሪ ልማት ዕቅድ ለማሳካት ፣በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ፣ በሀገሪቱ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ነባራዊ ሁኔታና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች መሠረት በማድረግ ፖሊሲውን መሠረት በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱ በርካታ የኢንዱስትሪ ስትራቴጅዎች እንዲቀረፁ ማድረጉን ጠቁመዋል።

በተቀናጀ እና በተናበበ አመራር የአምራች ኢንዱስትሪውን ማነቆዎች ለመፍታት፣ ተወዳዳሪነትና ምቹ ሁኔታ ለመፍጥር ሃገራዊ ሥርዓት እየተዘረጋ መሆኑን አንስተዋል።

አምራች ኢንዱስትሪው ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ስኬትና በልማት እቅዱ የታለመውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር እንዲወጣ ለማስቻል “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ወደ ተግባር ገብቶ በርካታ ለውጦችና ስኬቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልፀዋል።

Share this Post