"አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓይነት፣ በጥራትና በመጠን ምርቶቻቸውን እያሳደጉ ነው" (ክቡር አቶ መላኩ አለበል )

ሚያዚያ 13/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎሜትር ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓይነት፣ በጥራትና በመጠን ምርቶቻቸውን እያሳደጉ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ሩጫ በወንዶች አትሌት ገመቹ ዲዳ፤ በሴቶች አትሌት ጌጤ አለማየሁ አሸናፊ ሆነዋል። በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡት የ250 ሺህ ብር፣ የ150 ሺህ ብር እና የ100 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት፤ አምራች ኢንዱስትሪዎች በጥራትና በመጠን ምርቶቻቸውን እያሳደጉ ነው። ይህንን ለማስተዋወቅና ማህበረሰቡ የሀገር ውስጥ ምርቶችን እንዲጠቀም የኢትዮጵያ ታምርት የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተዘጋጅቷል።

የውድድሩ 80 በመቶ የሚሆኑት ተወዳዳሪዎች አምራች ኢንዱስትሪዎችና ሰራተኞች ናቸው ያሉት አቶ መላኩ፤ የአምራች ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅ እና ጤናማ ሠራተኛ ሊኖር ይገባል ብለዋል።

በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ከወጡት አሸናፊዎች በተጨማሪ እስከ አስር ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የገንዘብና በውድድሩ በመሳተፍ አትሌቶቻቸው በደረጃ ያጠናቀቁ ክለቦች የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post