በ2022 ኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትታይ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ሚያዝያ 11/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)በተሻሻለው አምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ዙሪያ ከሚኒስትር ዴኤታዎች እና ከፌዴራል ተቋማት ስራ ኃላፊዎች ፣ ከአምራች ኢንዱስትሪ የዘርፍ ማህበራት አመራሮች ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በ2022 ኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትታይ እየተሰራ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ።

ሀገሪቱ ያላትን ዕምቅ አቅም ለመጠቀም የሚያስችል፣ ከዘርፉ ተለዋዋጭ ባህሪያት ጋር የተጣጣመ እንዲሁም የአምራች ዘርፉን ሊመራ የሚችል ወጥና ሁሉን አቀፍ የአምራች ዘርፍ ፖሊሲ በማውጣት ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

በዋናነት ትኩረት ከተደረገባቸው መካከል ገበያ መር ፣ በግሉ ዘርፍ የሚመራ፣ ግልፅ የመንግስት ሚና የተቀመጠበት ፣ የኢንዱስትሪ ክላስተር፣ ለወጪና ተኪ ምርት የተመጣጠነ ትኩረት የሰጠ እንዲሁም ለዘላቂ አምራች ኢንዱስትሪ ልማት እና የተጣጣመ የሕግ ማዕቀፍ እንዲሆን መድረጉን ጠቁመዋል።

የምርት ልማትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የኢንዱስትሪ ክላስተር አሰራር የተከተለ፣ በተጠናከረ የግብዓት ምርት ልማት ትስስር የሚደገፍ፣ ለወጪ ንግድና ለተኪ ምርት ልማትና ግብይት እንዲሁም ለምርት ጥራት ሥራ _ አመራር ትኩረት የሚሰጥ የፖሊሲ መሆኑን አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ።

የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ለማሳደግ በኢንዱስትሪ ባህል እና በሥራ አመራር ክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል ማቅረብ ፣ የቀረበውን የሰው ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችል ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሩ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የምርት ሥርዓት ለማሻገር እንደሚሰራ አስረድተዋል ።

ፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነት ለማድረግ የተጠናከረ የብድር አቅርቦት፣ የውጪ ምንዛሬ ፣ የመድን ሽፋን እና ባንክ-ነክ ያልሆኑ ሌሎች የፋይናንስ ምንጮችን ለመጠቀም ትኩረት መደረጉን አስረድተዋል ።

ማክሮ ኢኮኖሚና የቢዝነስ ሥነ- ምህዳር መነሻ በማድረግ የተረጋጋና ተገማች የማክሮ ኢኮኖሚና አስቻይ የቢዝነስ ሥነ- ምህዳር መፍጠር የሚያስችል መሆኑን አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል ።

Share this Post