የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚደግፍ የመግባቢያ ሰነድ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር ተፈረመ

ሚያዚያ 13/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (JICA) ጋር

የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴን ተግባራዊ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩረቱን ያደረገው ፕሮጀክት ለቀጣይ አራት አመታት የሚቆይና የቴክኒካል ፣ የፖሊሲ እና የአቅም ግንባታ ድጋፎችን እንደሚያካትት ተጠቁሟል፡፡

ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የእውቀት ፣ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፎችን ከኤጀንሲው እንጠብቃለን ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ይህም የእወቅትና የቴክሎጂ ሁኔታ በእድገትና ተወዳዳሪነት ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ በመሆኑ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ዋና ተወካይ (ወክለው ስምምነቱን የፈረሙት) ኬንሱኬ ኡሺማ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማምጣት ከጀመረቻቸው እንቅስቃሴዎች መካከል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለውጥ ለማጣት የጀመረችውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንደሚደግፉና አስፈላጊውን የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤትን፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶችና ማህበራትን የማጠናከር አቅም እዳለው ተጠቁሟል፡፡

Share this Post