አምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የግል ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ሁለንተናዊ ብልጽግናን እናረጋግጣለን:: (አቶ ሀሰን መሀመድ)

ግንቦት 8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ከቻይና ሹኒ (SHUNY) ግዛት ተወክለው የመጡ ባለ ስልጣናትን አወያዩ፡፡

አቶ ሀሰን በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የግል ኢንቨስትመንትን በማበረታታት ኢንቨስተሩንም ሆነ የሀገሪቱን ዜጎች ለማበልጸግ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን በውይይታቸው ገልጸዋል፡፡

የቻይና ልኡካንም በበኩላቸው ኢትዮጵያ ሰፊ የህዝብ ቁጥር ያላት ሀገር እንደ መሆኗ መጠን ጥሩ የገበያ ሁኔታ ስለሚኖር የቻይና ባለሀብቶች በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመሰማራት ደስተኛ እንደሚሆኑ አብራርተዋል፡፡

በመጨረሻም ከቤጅንግ ሹኒ ግዛት ባለሀብቶች ጋር በትብብር በመስራት የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post