የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለሚዲያ ተቋማት የምስጋና መርሀ ግብር አካሄደ ።
ሰኔ 18/2018ዓ.ም(ኢሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከረሃብ ነፃ ዓለም እና የኢትዮጵያ ታምርት ኤከስፖ 2017 ስኬታማነት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተቋማት፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የዕውቅና ሽልማት አበረከተ፡፡
የዕውቅና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስቴር አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ሀገር የተሰጠውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ያከናወናቸውን ሁለት ትላልቅ ሁነቶች የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ በማስቻል በስኬታማነት እንዲያጠናቅቅ የበኩላቸውን ላበረከቱ አካላትን አመስግነዋል ።
አንደ ሃገር አኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ እና ሃገራዊ ብልፅግን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ሰኬታማ ለማድረግና ያለምነው ቦታ ለመድረስ አምራች ኢንዱስትሪው ላይ ጠንክረን መሰራት አለብን ብለዋል ።
የምንሰራቸው ስራዎች ህዝብ ዘንድ እንዲደርሱና ማህበረሰቡ የበኩሉን አዎንታዊ ሚና እንዲጫዎት ለማስቻል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተግባር ወሳኝ በመሆኑ ዘርፉ የሚመራበት የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር የገባ መሆኑን የገለፁት አቶ መላኩ ስትራቴጅው አምራች ኢዱስትሪዎችን ለማስተዋወቅ፣ ትስስራቸውን ለማጎልበት፣ በሃገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገፅታን ለመገንባት፣ የዕውቀት ሽግግር ለማምጣት፣ የልምምድ ልውውጥ ለማካሄድ፣ የገበያ መዳረሻዎችን ለማስፋት፣ ዘርፉን የተመለከቱ መረጃዎችን ለማሰራጨት ፣የምርቶች ማስታወቂያ ኤግዚቢሽንና ኤክስፖዎችን ለማዘጋጀት እና ጠንካራ መሰተጋብራዊ ግነኙነት እዲኖር ሚናው ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል ።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን ስኬታማ ዓለማቀፍ ሁነቶችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለህዝብ በማድረስ ጉልህ ሚና ለተጫወቱ 21 የሚዲያ ተቋማት ማለትም ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጀት፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ፣ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬት፣ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ፣ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን፣ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (ebs)፣ለአባይ ቴሌቪዥን ፣ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ፣ ለአሃዱ ሬዲዮና ቴሌቪዥን፣ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ፣ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ፣ መናኸሪያ ሬዲዮ ፣ ለጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ፣ ለድሬ ትዩብ ፣ ለቲክቫህ፣ ስፑትንኪ ኢትዮጵያ ፣ቃና ቲቪ፣ ሪፖርተር ጋዜጣና ካፒታል ጋዜጣ እውቅና ሰጥቷል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት