በድህረ_ እውነት አለም ላይ ለትውልድ የሚበጀውንና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድገውን መረጃ ተደራሽ ማድረግ መቻል ትልቅ አርበኝነት ነው (የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል)

ሰኔ 21/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በበላይነት ሲመራቸው ለነበሩ ሁለት ትላላቅ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሚዲያና ኮሙኒክሽን ተቋማት ባደረገው የእውቅና እና ምስጋና መርሃ-ግብር ላይ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ እንደ ሀገር የተካሄዱ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ እና ከርሃብ አልባ አለም ጉባዔ የተመለከቱ መረጃዎችን በማቅረብ አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያ አጀንዳ እንዲሆን በማድረግ ፣ ጥራት ያለው መረጃ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያድግ ትልቅ ሚና መጫወታቸውን ጠቁመው በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመጪው ትውልድ ጉዳይ በመሆኑ ይመለከተኛል በሚል በባለቤትነት ስሜት ሲመሩ እንደነበር ጭምር ተናግረዋል፡፡

በአንድ አገር ውስጥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማስፋፋት የተመቸ ከባቢያዊ ሁኔታ እና የባህል ግንባታ መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት አቶ መላኩ ይህም የአመለካከት ለውጥ በማሻሻል የሚመጣ በመሆኑ ከግንዛቤ በማስገባት የኮሙኒ ስራዎችን ውጤታማ በሆነና በተናበበና በተቀናጀ አግባብ ለማከናውን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን አስረድተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመጀመሪያ ሶስት አመታት በትኩረት መስክ የተቀመጠውን የግንዛቤ መፍጠር ስራ በተሟላ ሁኔታ ተሳክቷል ያሉት ሚኒስትሩ ይህም እንደተቋም ከተሰራው ስራ ጎን ለጎን የሚዲያ ተቋማት ትብብር፣ ሃሳብን በመግዛትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የነበራቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄው አስፈላጊው ግንዛቤ የመፍጠር የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አድርጓል ብለ

ዋል፡፡

ባለው ነባራዊ ሁኔታ በአለም፣ በሀገራችን ፣በተቋማት እና በየአካባቢው በርካታ የታሰቡና ያልታሰቡ የሃሰት መረጃዎች ማለትም ምርታማነት የማይጨምሩ፣ የማህበረሰቡን የጋራ እሴት የሚጎዱ፣ ልማታዊነትን የማያመጡ፣ የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠብቁ በርካታ ጎጂ ሃሳቦች በሚናኙበት የድህረ እውነት አለም ላይ እንገኛለን ያሉት አቶ መላኩ በእንዲህ አይነት ጊዜን ተጋፍጦ የራሳቸውን ሃሳብ ፣ለትውልድ የሚበጀውን ፣ምርትና ምርታማነት የሚያሳድገውን ፣የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት የሚያስችለውን፣ ሉዓላዊነት የሚያስከብረውን ሃሳብ በድፍረትና በሙሉ አቅም እንዲሁም በእውቀት ላይ የተመረኮዘ መረጃን ለህብረተስብ ተደራሽ ማድረግ ለሀገር ትልቅ አርበኝነት ነው በዚህም የሚዲያ ተቋማት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽ ምስጋናዬ የላቀ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post